Tenders

 

Type: Construction

 

Organization: በደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት

Dead Line: 2017-03-26

 

Tender Detail:

 

 

 

 

በደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በጉራጌ፣ በዳውሮ እና ቤንችማጂ ዞኖች ውስጥ የማሰራጫ ቤቶች ማለትም ትራንስሚተር ቤት፣ ጄነሬተር ቤት፣ ጥበቃ ቤት፣ ደረቅ መፀዳጃ ቤት እና ዙሪያ አጥር 50 ሜትር በ50 ሜትር ግንባታ ሥራ ህጋዊ ተጫራቾች አወዳድሮ በግልፅ ጨረታ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

 

በዚሁ መሠረት፡-

 

  1. ደረዳቸው GC/BC- 7 እና ከዛ በላይ የሆኑ፣
  2. ፍቃዳቸውንና ከኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የምዝገባ ሰርተፍኬታቸውን ለ2009 ዓ.ም ያሳደሱ የግብር መለያ ቁጥር ያላቸውና ለተጨማሪ ለ2009 ዓ.ም ያሳደሱ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸውና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡና የዘመኑ ግብር የከፈሉ፣
  3. ተጫራቾች ለሰራው የተዘጋጀውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ30 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ለእያንዳንዱ ዶክመንት የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ቀናት የድርጅቱ ግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ደ/የስራ ሂደት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፣
  4. ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና ብር 30,000  (ሰላሳ ሺህ ብር) ከቴክኒካል ኦሪጅናል ሰነድ ጋር አሸገው ማቅረብ አለባቸው፣
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን የቴክኒካል እና ፋይናንሻል ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ እያንዳንዳቸው ለየብቻ በሰም በታሸገ ኢንቭሎፕ በማድረግ ቴክኒካል ሰነድ ፋይናንሻሉን ‹‹ፋይናንሻል ሰነድ›› በማለት እና ጠቅላላውን በአንድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በ31ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00-6፡00 ሰዓት ድርጅቱ ለዚሁ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ መክተት አለባቸው፣
  6. 31ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፣
  7. ጨረታው በ31ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00- 6፡00 ሰዓት መ/ቤቱ የግ/ፋይ/ንብ/አስ/ደ/ስራ ሂደት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በመክተት ይታሸግና በዚያው እለት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፣
  8. አንድ ተቋራጭ አንድ የጨረታ ሰነድ ብቻ መግዛት አለባቸው፣
  9. አንድ ተጫራች መወዳደር የሚችለው ከላይ ከተገለጸው ከአንድ ባቻ ነው፣
  10. ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፣
  11. ድርጅቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡ 046 220 47 50 / 046 221 13 51 / 046 822 39 80