Tenders

 

Type: Multiple Items

 

Organization: አዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል

Dead Line: 2017-03-10

 

Tender Detail:

 

 

 

አዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል ለሕዝብ መድኃኒት ቤት፤ የኮፒ ፕሪንተር ማሽን፣ የላብራቶሪ ፣ የውበት መጠበቂያ ግብዓቶችን እና የህክምና መገለገያ መሣሪያዎችን በጋዜጣ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በሥራ በመስኩ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ የንግድ  ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መከፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

  2. ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፣

  3. ተጫራቾች ጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋ 2% ከባንክ ሲፒኦ /በባንክ ጋራንት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

  4.   የጨረታ ሰነዱ አዳሬ ሆስፒታል ቢሮ ቁጥር 3 በማቅረብ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ብር 50 (ሀምሳ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፣

  5. ጨረታ ሰነዱ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ  አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ (ቴክኒካል እና ፋይናንሻል) በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት አዳሬ ሆስፒታል ቢሮ ቁጥር 3 ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣

  6. ጨረታው በዚሁ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) በተገኙበት በቢሮ ቁጥር 3 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን ቅዳሜ (እሁድ) ከሆነ በሚቀጥለው ሰኞ ጨረታው የሚገባበትና የሚከፈትበት ቀን ይሆናል፡፡ የበዓል ቀን ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው ሥራ ቀን ይከፈታል፡፡ የጨረታው ቴክኒካል ግምገማ መስፈርት መሠረት ብቻ ይሆናል፡፡ ቴክኒካል ግምገማ ያለፋ ድርጅቶቸ ብቻ ለፋይናንሻል ይጋበዛሉ፡፡

  7. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

  8. ለተጨማሪ መረጃ፡-  046 221 16 61  / 046 220 81 86

  9. በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር አዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል