Tenders

 

Type: Autos

 

Organization: የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/ መንግሥት ጠቅላይ ፍ/ቤት / ሀዋሳ

Dead Line: 2017-03-14

 

Tender Detail:

 

 

 

የደ/ቡ/ብ/ህ/ክ/ መንግሥት ጠቅላይ ጽ/ቤት በ2009 በጀት ዓመት የሚገለገልባቸው ተሸከርካሪዎች /መኪናዎች/የሚጠግን ጋራዥ በጨረታ ለማወዳደር ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው፡፡

    1. ተጫራቾች በተሸከርካሪ ጥገና የአገልግሎት ዘርፍ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
    2. ተጫራቾች በጨረታው ለመካፈል በሀገር ውስጥ አገልግሎት ሰጪዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
    3. የታደሰ የሙያ ፍቃድ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
    4. የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማስረጃ ካላቸው ማቅረብ የሚችሉ፣
    5. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ተመዝገቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፣
    6. በቂ ኢንሹራንስ ሽፋን ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
    7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100  አንድ መቶ ብር / በመክፈል ከመቤታችን ግ/ፋ/ን/አስ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 209 በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
    8. ማንኛውም ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ በመ/ቤቱ ስም በባንክ የተመለከተ ሲፒኦ ከኦርጅናል ጨረታው ሠነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ አለበት፡፡
    9. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ የቴክኒካልና ፋይናንሻል ለየብቻ ኦርጅናልና ኮፒ በመለየት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ አንስቶ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፣
    10. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፡፡
    11. ተጫራቾች የተሸከርካሪ መጠገኛ ጋራዥ የብቃት ደረጃ ማረጋገጫ ለቀላል ሁለገብ ጥገና ጋራዥ 3ኛ ደረጃ እና ከዚያ በላይ እንዲሁም ለመካከለኛና ከባድ ተሸከርካሪ ሁለገብ ጥገና ጋራዥ 3ኛ ደረጀ እና ከዚያ በላይ ያገኘና ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፣
    12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ወይም በሙሉ በከፊል የመሠረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡
    13. ለተጨማሪ መረጃ፡- 046 221 25 71 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
    14. የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/ መንግሥት ጠቅላይ ፍ/ቤት / ሀዋሳ