Tenders

 

Type: Autos

 

Organization: ብሔራዊ የኢትዮጵያ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ.

Dead Line: 2017-03-17

 

Tender Detail:

 

 

 

ብሔራዊ የኢትዮጵያ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ.) የካሣ ክፍያ ፈጽሞ የተረከባቸውን ከዕዳ ና ዕገዳ ነፃ የሆኑ የተጎዱ ተሽከርካሪዎች እና ጋቢናዎች እንዲሁም ሁለት የብስኩት መ ጋገሪያ ማሽኖች (Rack Oven MIWI) ባሉበት ሁኔታ በጨረታ ይሸጣል::

ተጫራቾች ከየካቲት 29 ቀን 2009 ዓ.ም. እስከ ኅመጋቢት 8 ቀን 2009 ዓ.ም. በሥራ ሰዓት የጨረታ ሰነድና የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) ከፍለው መውሰድ ይችላሉ::

ተጫራቾች ንብረቶቹን ከየካቲት 29 ቀን 2009 ዓ.ም. ጀምሮ በሥራ ሰዓት እስከ መጋቢት 8 ቀን 2009 ዓ.ም. 11፡0ዐ ሰዓት ድረስ ከሃና ማርያም ወደ ቃሊቲ አደባባይ በሚወስደው ቀለበት መንገድ ከቻይና ጠጠር መፍጫ ፊት ለፊት በስተግራ በኩል የአጠና መሸጫ አጠገብ ከሚገኘው የኩባንያው የንብረት ማከማቻ መጋዘን ውስጥ በአካል ተገኝተው መመልከት ይችላሉ::

የጨረታ መነሻ ዋጋው 15% ቫት ያላካተተ ወይም ያልጨመረ መሆኑን እየገለፅን ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ቫት ሳይጨምሩ በዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ላይ በመሙላት በ ብሔራዊ የኢትዮጵያ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ.) ወይም በእንግሊዝኛ NATIONAL INSURANCE CO. OF ETHIOPIA (S.C.) ስም በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ጋር በኤንቨሎፕ በማሸግ ከየካቲት 29 ቀን 2009 ዓ.ም. እስከ መጋቢት 8 ቀን 2009 ዓ.ም. 11 ሰዓት ላንቻ ፊት ለፊት ዘፍኮ ሕንፃ በሚገኘው በዋናው መ/ቤት ውል ክፍል ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ::

ጨረታው መጋቢት 9 ቀን 2009 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡0ዐ ሰዓት ጀምሮ በኩባንያው ንብረት ማከማቻ ግቢ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡:

ማሳሰቢያ፡- አሸናፊ ተጫራቾች ለአሸነፉት ንብረት ክፍያ ሲፈፅሙ በጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ባቀረቡት ዋጋ ላይ 15% ቫት የሚጨምሩ መሆኑን እንገልፃለን፡:

ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ ለተሸናፊዎች ሙሉ በሙሉ የሚመለስ ሲሆን ለአሸናፊዎች ግን ከሚገዙበት ዋጋ ጋር ይታሰባል:: ተጫራቾች ለተጫረቱበት ንብረት አሸናፊነታቸው ከተገለፀበት ዕለት ጀምሮ በ8 የሥራ ቀናት ውስጥ ክፍያውን አጠናቀው ንብረቱን ካልተረከቡ ያስያዙት ገንዘብ ለኩባንያው ገቢ ሆኖ አሸናፊነታቸው ይሰረዛል:: የተሽከርካሪው የስም ማዛወሪያ በጨረታ አሸናፊው የሚሸፈን ይሆናል:: ከቀረጥ ነፃ የገባ ተሽከርካሪ እና የብስኩት መጋገሪያ መሽኖች ለአሸናፊው ተጫራች የምናስረክበው የጉምሩክ ቀረጥ ከፍሎ ማስረጃ ሲያቀርብ ብቻ ነው::ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም::

ስልክ 011-466-11-29/0114-65-56-05