Tenders

 

Type: Services

 

Organization: የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን

Dead Line: 2017-03-28

 

Tender Detail:

 

 

 

 

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አዲስ ባሰገነባው የመዝናኛ ከበብ ለመስሪያ ቤቱ ሠራተኞችና ደንበኞች አገልግሎት የሚሠጥ ድርጅት ወይም ግለሰብ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሰጠት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በሥራ ዘርፋ የተሰማሩና ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ በውድድሩ መሳተፍ ይችላሉ፡፡

ይኸውም፡-


1. በሥራ ዘርፋ ህጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድን ጨምሮ ፣ የግብር ከፍይነት መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ወይም TOT (የሒሳብ መመዝገቢያ ማሽን) ምስክር ወረቀቶች ያላቸውና ኦርጅናል እና ኮፒዎቻቸውን አያይዘው መቅረብ መሆን አለባቸው፡፡

2. ዕጩ ተወዳዳሪዎች የመልካም ሥራ አፈፃጸም ቀድሞ ሲል ከሠሩባቸው ድርጅቶች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከመውጣቱ በፊት የተሰጣቸውን ኦርጅናልና ኮፒውን አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

3. ዕጩ ተወዳዳሪዎች የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል የመዝናኛ ክበብ አገልግሎት ግዥን አስመልክቶ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ቢሮ በአካል በመምጣት ይህ ማስታወቂያው አዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከሚወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ከመ/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 004 በመውሰድ የሚወዳደሩበትን የአገልግሎት ዝርዝር ዋጋ መሙላት የጨረታ ሰነዱን በታሸገ ኢንቨሎፕ ኦርጅናሉንና ኮፒውን ለየብቻ በማቅረብ ጉዳዩን አስመልክቶ በተዘጋጀውና በቢሮ ቁጥር 316 3ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡

4. ዕጩ ተወዳዳሪዎች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል ብር 2000.00 (ሁለት ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው፡፡ በሌላ መልክ የሚቀርበውን ዋስትና መ/ቤቱ እያስተናግድም፡፡

5. ጨረታው ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜ ወይም ዕሁድ እንዲሁም በበዓል ቀን ከዋለ በሚቀጥለው ሥራ ቀን በተመሳሳይ ቦታ እና ሰዓት በኮሚሽኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡

6. መስሪያ ቤቱ ውሃና መብራት እንዲሁም መሠረታዊ የመስሪያ ዕቃዎች፣ ፍሪጅ፣ የሻይ ማሽን ፣ ወንበርና ጠረጴዛ በነፃ ያቀርባል፡፡ የቤት ኪራይ 300 መቶ ብር ብቻ መሆኑን ያሳውቃል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በአሁኑ ጊዜ የሠራተኛ መዝናኛ ክበባችን መሠረታዊ የመስሪያ ዕቃዎች እንደ ፍሪጅ፣ የሻይ ማሽን፣ ወንበርና ጠረጴዛ የመሳሰሉት ናቸው፡፡

7. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

8. ስልክ ቁጥር፡- 011-15-86-49

9. አድራሻ ቦሌ መንገድ ደንበል ሲቲ ፊት ለፊት ኖክ ነዳጅ ማደያ ጎን

10. የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን