Tenders

 

Type: Multiple Items

 

Organization: የደቡብ ክልል እንስሳትና ዓሳ ሀብት ቢሮ

Dead Line: 2017-04-06

 

Tender Detail:

 

 

የደቡብ ክልል እንስሳትና ዓሳ ሀብት ቢሮ በስሩ ለሚገኘው ለሀዋሳ የዳልጋ ክብት አባላዘር ማምረቻ ማዕከል ለአባላዘር ምግብነት የሚያገለግል ብዛት Vial 50  Bovine sement Ezxtender በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በንግድ ዘርፋ የታደሰ ፈቃድ የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ማስረጃ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡

  • ተጫራቾች ለመጫረት የሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 0.5 % ገንዘብ የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ያስያዙበትን ማቅረብ አለባቸው፡፡
  • ተጫራቾች በቢሮው የተዘጋጀውን የተጫራቾች መመሪያና ዝርዝር መግለጫ (ስፔሲፊኬሽን) ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን 9፡00 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 50 በመክፈል ከቢሮው የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ቢሮ ቁጥር 42 መውሰድ ይችላሉ፡፡
  • ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ (ፕሮፎርማ) በመሙላት ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ የቴክኒካል እና ፋይናንሻል ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ እያንዳንዳቸው ለየብቻ በሰም በታሽገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ቴክኒካሉን ቴክኒካል ሰነድ ፋይናንሻሉን ፋይናንሻል ሰነድ በማለት እና ጠቅላላውን በአንድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግና ሲፒኦ ቴክኒካል ዶክሜንት ውስጥ በማድረግ በቢሮ የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ቢሮ ቁጥር 42 ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  • የጨረታውን ሳጥን የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 9፡05 ሰዓት ተጫራቾች/ተወካዮቻቸው በተገኙበት በቢሮው የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ቢሮ ቁጥር 42 ይከፈታሉ፡፡ ነገር ግን 15ኛው ቀን የሥራ ቀን ባይሆን ሳጥኑን የማሸጉም ሆነ የመክፈቱ ሰነ-ሰርዓት የሚከናውነው በቀጣዩ የሥራ ቀን ከላይ በተገለጸው ቦታና ሰዓት ይሆናል፡፡
  • ቢሮው ለዚሁ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊም ሆነ ሙሉ በመሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  • ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-  046 212 17 16
  • በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግሥት የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ቢሮ
  • ሀዋሳ