Tenders

 

Type: Machinary

 

Organization: የደቡብ መንገዶች ባለሥልጣን ታርጫ ዲስትሪክ ጽ/ቤት

Dead Line: 2017-04-16

 

Tender Detail:

 

 

 


የደቡብ መንገዶች ባለሥልጣን ታርጫ ዲስትሪክ ጽ/ቤት
በ2009 በጀት ዓመት በስሩ ላሉት ፕሮጅክቶች አገልግሎት የሚውል ፌሮ ብረትና ሌሎች ለግንባታ የሚውሉ ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም፡-

  1. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችለውን የዘመኑን ግብር የተከፈለበትን ከሚፈለገው አገልግሎት የተዛመደ የንግድ ስራ ወይም አገልግሎት ስራ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስከር ወረቀት በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

  2. ተጫራቾች ዋጋቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ የፋይናንሻል ፕሮፖዛሉን በተለያየ ፖስታ ለብቻው በማድረግ በተወዳደሩበት ሙያ ዘርፍ /ፍቃድ/ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

  3. ተጫራቾች ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከዲስትሪክቱ የቢሮ ቁጥር 4  መውሰድ ይችላሉ፡፡

  4. የጨረታው አሸናፊ የሚወሰነው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተመለከቱ መስፈርቶች መሰረት ሲሆን ጨረታውን ዜግነትን ሳይመለከት ለማንኛውም አቅራቢ ክፍት ነው፡፡

  5. አቅራቢዎች ጨረታውን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀ ሳጥን ገቢ የሚያደርጉት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስክ 15ኛው ቀን ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ድረስ ይሆናል፡፡ ጨረታው በዚያኑ ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡

  6. ተጫራቾች የጠቅላላ ዋጋ 1% የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከዚህ ወጪ በኢንሹራንስ ወይም ሌላ መልክ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም፡፡

  7. ተጫራቾች በጨረታው ደንብና መመሪያ መሰረት ጨረታችውን ማቅረብ አለባቸው፡፡ ከጨረታው ደንብና መመሪያ ውጪ የሚቀርብ ማንኛውም ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡

  8. ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ፡፡

  9. የታርጫ ዲስትሪክት

  10. አቅ/ንብ/አስ/ደጋ/የስራ ሂደት

  11. ፖስታ ሳጥን ቁጥር 60

  12. የስልክ ቁጥር 0913031711 ፤ 0473450123 ፤ 0938710390 ፤ ፋክስ 047 345 03 41

በደቡብ መንገዶች ባለስልጣን ታርጫ ዲስትሪክት ጽ/ቤት