Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 174

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 176

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 216

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 218

ግቦቼ ላይ ለመድረስ ምን ላድርግ?

ግቦቼ ላይ ለመድረስ ምን ላድርግ?

 

Image result for success

 

ከሚከተሉት ውስጥ የምትፈልገው የትኛውን ነው?

□ ይበልጥ በራስ መተማመን

 

□ ተጨማሪ ጓደኞች ማግኘት

 

□ የበለጠ ደስተኛ መሆን

 

ሦስቱንም ነገሮች ማሳካት ትችላለህ! እንዴት? ግቦች በማውጣትና ያወጣሃቸው ግቦች ላይ በመድረስ ነው። ቀጥሎ የቀረቡትን ሐሳቦች ተመልከት፦

 

ይበልጥ በራስ መተማመን። ትናንሽ ግቦችን አውጥተህ እነዚያ ላይ መድረስ መቻልህ ትላልቅ ግቦችንም ብታወጣ ልትደርስባቸው እንደምትችል እንድትተማመን ያደርግሃል። እንዲሁም በየዕለቱ የሚያጋጥሙህን ፈታኝ ሁኔታዎች ለምሳሌ የእኩዮችን ተጽዕኖ ለመቋቋም የሚያስችል በራስ የመተማመን ስሜት ታዳብራለህ።

 

ተጨማሪ ጓደኞች ማግኘት። ብዙዎች ጓደኝነት መመሥረት የሚፈልጉት ሊደረስበት የሚችል ግብ ካላቸው ሰዎች ጋር ነው፤ እንዲህ ዓይነት ሰዎች ምን ማድረግ እንደሚፈልጉ የሚያውቁ ከመሆኑም ሌላ የፈለጉትን ለማግኘት ጥረት ያደርጋሉ።

 

የበለጠ ደስተኛ መሆን። እውነቱን እንነጋገር ከተባለ፣ ነገሮች አሰልቺ ከሆኑብህ ወይም ደግሞ ነገ የተሻለ ሕይወት እንደሚኖርህ እያለምህ እጅህን አጣጥፈህ ከተቀመጥህ ደስተኛ እንደማትሆን የታወቀ ነው። በሌላ በኩል ግን ግብ ስታወጣና ያወጣኸው ግብ ላይ ስትደርስ አንድ ነገር በማከናወንህ ደስ ይልሃል። ታዲያ ግብ ለማውጣት ተዘጋጅተሃል? በሚቀጥሉት ገጾች ላይ ያሉት ሐሳቦች በዚህ ረገድ ይረዱሃል።*

 

✔ 1 ግብህን ለይ

 

1. ልታወጣቸው የምትችላቸውን ግቦች አስብ። ይህን ስታደርግ ያን ያህል መጨነቅ አያስፈልግህም። ይሳካል አይሳካም የሚለውን ሳታስብ ወደ አእምሮህ የመጡትን ግቦች በሙሉ ጻፋቸው። ቢያንስ 10 ግቦችን ለመጻፍ ሞክር።

 

2. የጻፍካቸውን ግቦች ገምግም። ይበልጥ የሚያጓጉህ የትኞቹ ግቦች ናቸው? በጣም ተፈታታኝ እንደሆኑ ያሰብካቸውስ? ትልቅ ነገር እንዳከናወንክ የሚሰማህ የትኞቹ ግቦች ላይ ብትደርስ ነው? ከፍ አድርገህ የምትመለከተው ግብ ላይ መድረስ አብዛኛውን ጊዜ ቀላል እንደሚሆንልህ አስታውስ።

 

3. ቅደም ተከተል ስጣቸው። መጀመሪያ ልትደርስበት ከምትፈልገው ጀምረህ ግቦችህን በቅደም ተከተል ደረጃ ስጣቸው።

 

✔ 2 እቅድ አውጣ

 

ለመረጥከው ለእያንዳንዱ ግብ የሚከተለውን አድርግ፦

 

ግብህን ጻፍ።

 

ወላይታ ሶዶ ለመሄድ ስላሰብኩ ወላይትኛ እማራለሁ

ቀነ ገደብ አብጅ። ቀነ ገደብ የሌለው ግብ ሕልም ሆኖ ይቀራል!

 

ሐምሌ 1

የምትወስዳቸውን እርምጃዎች መዝግብ።

 

እርምጃዎች

1. ወላይትኛ መማሪያ መጽሐፍ ማግኘት።

2. በየሳምንቱ አሥር አዳዲስ ቃላትን መማር።

3. ሌሎች ሰዎች ወላይትኛ ሲናገሩ ማዳመጥ።

4. በቋንቋው ሰዋስው እና በቃላት አጠራር ረገድ አንድ ሰው እንዲያርመኝ መጠየቅ።

ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን አስብ። ከዚያም የመፍትሔ ሐሳብ አስፍር።

 

ቁርጥ ውሳኔ አድርግ። ግብህ ላይ ለመድረስ የቻልከውን ሁሉ ለማድረግ ለራስህ ቃል ግባ። ከዚያም ፊርማህንና ቀኑን አስፍር።

 

ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮች

ወላይትኛ የሚናገር ሰው በአካባቢዬ የለም

ችግሮቹን መወጣት የምችለው እንዴት ነው?

 

በወላይትኛ የተቀዱ ካሴቶችንና በዚህ ቋንቋ የሚተላለፉ ፕሮግራሞችን ማዳመጥ።

․․․․․ ․․․․․

ፊርማ ቀን

✔ 3 ተግባራዊ አድርግ!

ዛሬ ነገ አትበል። ‘ግቤ ላይ ለመድረስ ዛሬ ምን ማድረግ እችላለሁ?’ እያልክ ራስህን ጠይቅ። እርግጥ ነው፣ ግብህ ላይ ለመድረስ የሚያስፈልግህን እያንዳንዱን ዝርዝር ነገር አልጻፍክ ይሆናል፤ ይህ ግን ወደ ግብህ የሚያደርስህን እርምጃ መውሰድ እንዳትጀምር እንቅፋት ሊሆንብህ አይገባም። “የነፋስንና የአየርን ጠባይ የመስተካከል ሁኔታ የሚጠባበቅ ሰው ዘሩን በወቅቱ አይዘራም፤ መከሩንም በጊዜው አይሰበስብም።” ትንሽ ቢሆንም እንኳ ዛሬ ልታከናውነው የምትችለውን ነገር አድርግ።

 

ግቦችህን በየቀኑ ገምግም። እያንዳንዱ ግብ ለአንተ አስፈላጊ የሆነበትን ምክንያት መለስ ብለህ አስብ። እያንዳንዱን እርምጃ ስታጠናቅቅ ከአጠገቡ ✔ አድርግ ወይም የተጠናቀቀበትን ዕለት አስፍር።

 

በዓይነ ሕሊናህ ለማየት ሞክር። ወደፊት ግብህ ላይ ስትደርስ በዓይነ ሕሊናህ ይታይህ። ግብህ ላይ መድረስህ ምን ያህል እንደሚያስደስትህ አስብ። አሁን ደግሞ ወደ ግብህ ለመድረስ ስለሚያስችልህ ስለ እያንዳንዱ እርምጃ አውጠንጥን። ቀጥሎም እያንዳንዱን እርምጃ እየወሰድክ ተራ በተራ ስታጠናቅቅ በመጨረሻም ግብህ ላይ ስትደርስ ምን ያህል ልትደሰት እንደምትችል በዓይነ ሕሊናህ ለመሳል ሞክር። በል አሁን ግብህ ላይ ለመድረስ ታጥቀህ ተነሳ!

 

[የግርጌ ማስታወሻ]

 

እዚህ ላይ የቀረቡት ሐሳቦች በዋነኝነት ያተኮሩት በአጭር ጊዜ በሚደረስባቸው ግቦች ላይ ቢሆንም ነጥቦቹ ለረጅም ጊዜ ግቦችም ይሠራሉ።

 

ቁልፍ ጥቅስ

 

“የትጕህ ሰው ዕቅድ ወደ ትርፍ ያመራል።

 

ጠቃሚ ምክር

 

እያንዳንዱ ነገር እንዳቀድኩት ካልሆነ ብለህ በጣም አትጨነቅ። ግብህ ላይ ለመድረስ የሚረዱ ማስተካከያዎች በሚያስፈልጉህ ጊዜ ይህን ለማድረግ ፈቃደኛ ሁን።

 

ይህን ታውቅ ነበር?

 

ያወጣኸው ግብ ትልቅ ከሆነ ግቡ ላይ ስትደርስ የሚኖርህ ደስታም ያንኑ ያህል ከፍ ያለ ነው!

 

ምን ይመስልሃል?

 

● በአንድ ጊዜ በጣም ብዙ ግቦች ላይ መድረስ ይቻላል?

● ግብ ማውጣት ማለት ለእያንዳንዱ እንቅስቃሴህ እቅድ ማውጣት ማለት ነው?

ምንጭ፡- የወጣቶች ጥያቄ