Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 174

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 176

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 216

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 218

የሚመገቧቸው ምግቦች ከደም አይነት አንጻር ጠቀሜታ እና ጉዳት አላቸው።

አመጋገብዎ ከደም አይነት አንጻር ምን መምሰል አለበት?

 

 

 

የሚመገቧቸው ምግቦች ከደም አይነት አንጻር ጠቀሜታ እና ጉዳት አላቸው።

ሁሉም ምግቦች ለሰውነት እኩል ጠቀሜታ የላቸውም፤ ከዚህ አንጻር የሚመገቧቸው ምግቦች በሶስት ደረጃ ይመደባሉ።

በዚህም ከደም አይነት አንጻር በጣም ጠቃሚና አስፈላጊ፣ አስፈላጊ እና ለምግብነት የማይመከሩ ተብለው ተመድበዋል።

የመጀመሪያዎቹ ለሰውነት እንደ መድሃኒት የሚያገለግሉ ሲሆን ሁለተኛዎቹ ደግሞ አስፈላጊ የሚባሉና ቢመገቧቸው ጉዳት የማያስከትሉ ናቸው።

የመጨረሻዎቹ ደግሞ በመመገብዎ ጉዳት የሚያስከትሉ ሆነው ለሰውነት አስፈላጊ አይደሉም።

በአጠቃላይም ከደም አይነት አንጻር ሰዎች ምን አይነት አመጋገብ ቢከተሉ ይመረጣል የሚለውን ከዚህ በታች የተወሰነ መመልከት ይቻላል።

“A” ቢመገቧቸው የሚመከሩ፦ አትክልት፣ አሳና የአሳ ተዋጽኦ፣ ፍራፍሬ እና የጥራጥሬ ዘሮች በተለይም አናናስ እና ከጥራጥሬ ደግሞ ባቄላ ይህን የደም አይነት ለታደሉ ሰዎች እጅግ ወሳኝ ምግብ ነው።

መመገብ የሌለባቸው፦ ስጋ እና የስጋ ተዋጽኦ፣ ወተትና የወተት ተዋጽኦ እንዲሁም ከጥራጥሬ ደግሞ ስንዴ አይስማማቸውም።

“B”  ለምግብነት የሚመከሩ፦ ከዶሮ ውጭ ስጋ፣ ወተትና የወተት ተዋጽኦ፣ አትክልትና ፍራፍሬ፣ ከጥራጥሬ ባቄላ፣ እንቁላል፣ ትኩስ ጉበት እና ትኩስ ሻይ ይስማማቸዋል።

መመገብ የሌለባቸው፦ ምስር፣ በቆሎ፣ ሰሊጥ፣ ስንዴ እና ለውዝ ለዚህ አይነት የደም ባለቤቶች አይመከሩም።

“AB” መመገብ ያለባቸው፦ የተዘጋጀና ሙዳ ስጋ፣ አትክልትና አሳ፣ ወተትና የወተት ተዋጽኦ፣ ፍራፍሬ በተለይም እንደ አናናስ ያሉት እና ባቄላን ከጥራጥሬ ይመገቡ።

መመገብ የሌለባቸው፦ ቀይ ጥሬ ስጋ፣ በቆሎ፣ ቦሎቄና የቦሎቄ ዘሮች እንዲሁም የቅባት እህሎችን ከገበታ ቢያስወግዱ ይመረጣል።

“O” መመገብ ያለባቸው፦ በፕሮቲን የበለጸጉ፣ የተዘጋጁ ስጋዎችና አሳ፣ ለውዝ፣ ቀለማቸው ቢጫ እና ቀላ ያሉ የአትክልት ዘሮች እና ፍራፍሬ ቢመገቡ ይመከራል።

በተለይም ቀይ ስጋ፣ አሳ፣ ጨዋማ ምግቦች እና ትኩስ ጉበት ተመራጭ ናቸው።

መመገብ የሌለባቸው፥ ስንዴ፣ በቆሎ፣ ቦሎቄ፣ ምስር እና ጎመን ለዚህ አይነት ሰዎች ለገበታ የማይመረጡ ምግቦች ናቸው።

ከደምዎ አይነት አንጻር ሲመገቡ የታዘቡት ካለ ከላይ ከቀረበው ጋር ያነጻጽሩት።

ምንጭ፡- (ኤፍ ቢ ሲ)