Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 174

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 176

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 216

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 218

ተመራማሪዎች እድሜያችን እየገፋ ሲሄድ እንድናረጅ የሚያደርገውን ሂደት ??

የሰው ልጅ እንዳያረጅ ማድረግ ችለናል ይላሉ ተመራማሪዎች

 

ተመራማሪዎች እድሜያችን እየገፋ ሲሄድ እንድናረጅ የሚያደርገውን ሂደት ለማስቆም የሚያስችል አዲስ መላ አግኝተናል ይላሉ።

እርጅናን ማስቆም ችለናል የሚሉን በአሜሪካ የካሊፎርኒያ ቴክኖሎጂ ኢኒስቲቲዩት እና የሎስ አንጀለስ ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ካሊፎርኒያ ተመራማሪዎች ናቸው።

እንዴት ማለት ጥሩ ነው፥ ተመራማሪዎቹ ለህዋሶቻችን ሀይል በመስጠት ይታወቃል በሚባለው “ማይቶኮንዶሪያ” ላይ ባደረጉት ምርምር ነው ይህን ማግኘት የቻልነው ሱሉም ምላሽ ይሰጣሉ።

የሰው ልጅ ህዋሶች /ሴሎች/ ስራቸውን በአግባቡ መስራት ሲያቆሙ እና ሲሞቱ ማርጀት ይጀምራል።

ተመራማሪዎቹ አሁን ባገኙት አዲስ የምርምር ውጤት ግን የሰው ልች ህዋስ ስራ እንዳይዛባ እና እንዳይሞት ማድረግ እንደቻሉ ነው ያስታወቁት።

ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል…?

እንያንዳንዱ ህዋሳችን የራሱ የሆነ ሀይል ሰጪ ወይም በተለምዶ “ባትሪ” ያለው ሲሆን፥ ይህም “ማይቶኮንዶሪያ” በመባል ነው የሚታወቀው።

በአንድ ህዋስ ስራውን ለማከናወን በውስጡ በ100 ሺህ የሚቆጠር “ማይቶኮንዶሪያ” እንዳሉት ይታወቃል።

ነገር ግን አንድ የማናውቀው ነገር አለ የተባለ ሲሆን፥ ይህም የህዋሶቻችን ባትሪ በመባል የሚታወቁት “ማይቶኮንዶሪያ” ድንገት ስራ ሊያቆሙ ይችላሉ።

በዚህም የተነሳ እያንዳንዱ ህዋስ ጤናማና የተመጣጠነ ሀይል የሚሰጡ እንዲሁም ስራ ያቆሙ ማይቶኮንዶሪያ በውስጡ ይይዛል።

ህዋሳችን ስራ ያቆመ ማይቶኮንዶሪያን በራሱ መንገድ የሚያስወግድ ሲሆን፥ ይህም “ማይቶግራፊ” በመባል ይታወቃል።

ታዲያ እድሜያችን እየገፋ ሲሄድ ህዋሶቻችን ስራ ያቆሙትን ማይቶኮንዶሪያ ማስወገዱ ላይ ላይ እና አዳዲስ የማምረቱ ሂደት ላይ እየተዳከሙ ይሄዳሉ ተብሏል።

በዚህም ምክንያት ነው እድሜ እየተጫጫነን፣ ነገሮችን በቀላሉ መስራት እያቃተን እና እያረጀን የምንመጣው ይላሉ ተመራማሪዎቹ።

ተመራማሪዎቹ አሁን ያገኙት አዲስ ዘዴ ግን ህዋሶቻች ስራ ያቆሙትን ማይቶኮንዶሪያ የሚያስወግዱበትን መንገድ የሚያጠናክር እና አዲስ ማይቶኮንዶሪያ እንዲያመርቱ በማድረግ ለማመጣጠን የሚያችል ነው ተብሏል።

 

ያገኙትን አዲስ ቴክኒክም በጡንቻ ህዋስ ላይ የሞከሩት ሲሆን፥ በዚህም የእርጅና ሂደቶችን ማስቆም እንደቻሉ አስታውቀዋል።

ግኝቱ ህዋሶቻችን ላይ ከፍተኛ ለውጥ የሚያመጣ ሲሆን፥ ይህም ህዋሶቻችን የወጣትነት ጥንካሬ እንዲኖራቸው እና ሀይል የማመንጨት አቅማቸው እንዲጨምር ያደርጋል ይላሉ የባዮሎጂካል እንጂነሪንግ ፕሮፌሰር በሩስ ሄይ።

 

መች ተግባራዊ ይሆናል…?

ፕሮፌሰር በሩስ ሄይ “አሁን የተገኘውን አዲሱን የእርጅና መከላከያ ዘዴ ተግባራዊ የምናደርግበት ጊዜ ገና ነው” ያሉ ሲሆን፥ “ነገር ግን ከምታስቡት በላይ ፈጥኖ ስራ ላይ ይውላል” ብለዋል።

 

ምንጭ፦ www.huffingtonpost.co.uk