Tenders

 

Type: Construction

 

Organization: የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ

Dead Line: 2016-06-19

 

Tender Detail:

 





የሀዋሳ ከተማ ጸጥታና አስተዳደራዊ ጉዳይ መምሪያ ለምስራቅ ክ/ከተማ ለሀይቅ ዳር ክ/ከተማ እና ለባህል አዳራሽ ክ/ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤቶች ቢሮ የሚሆን በየክፍለ ከተማ  2 ህንጻ ግንባታ ለማካሄድ በመስኩ የተሰማሩ ልምድ ያላቸውን ተቋራጮችን በጨረታ አወዳድሮ ቀጥሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

  1. በዚህ መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ኮንትራክተሮች መወዳደር ይችላሉ፣ በኮንስትራክሽን ዘርፍ የተሰማሩ ደረጃ 5፣  6 እና ከዚያ በላይ ያላቸው፣

  2. በስራ መስኩ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የተቋራጭነት ብቃት ማረጋገጫ ምስክረ ወረቀት፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

  3. ተጨማሪ እሴት ታክስ () ተመዝጋቢ የሆኑ፣

  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 1 ከባንክ ሲ.ፒ.ኦ /ባንክ ጋራንቲ/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣

  5. የጨረታ ሰነዱ ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ ቢሮ ቁጥር 3 በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 /ለሃያ አንድ/ ተከታታይ ቀናት ብር 200 /ሁለተ መቶ  ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡

  6. የጨረታ ሰነዱ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦሪጂናልና ሁለት ኮፒ /ቴክኒካል እና ፋይናንሻል/ በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን ከቀኑ 4፡30-6፡00 ሰዓት በፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ ቢሮ ቁጥር 6 ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

  7. ጨረታው ከዚሁ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮ ቁጥር 6 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው ሰኞ ጨረታው የሚገባበትና የሚከፈትበት ቀን ይሆናል፡፡ የበዓል ቀን ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው ስራ ቀን ይከፈታል፡፡ የጨረታው ቴክኒካል ግምገማ በጨረታ ሰነዱ በዝርዝር በተቀመጡ የቴክኒካል ብቃት ግምገማ በጨረታ ሰነዱ በዝርዝር በተቀመጡ የቴክኒካል ብቃት ግምገማ መስፈርት መሰረት ብቻ ይሆናል፡፡ ቴክኒካል ግምገማ ያለፉ ድርጅቶች ብቻ ለፋይናንሻል ይጋበዛሉ፡፡

  8. መስሪያ ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0462209963 / 0462200665/

0462211661

ፋክስ ቁጥር 0462208532 ፖ.ሣ.ቁጥር 02

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ

ሀዋሳ