Tenders

 

Type: Construction

 

Organization: በባሌ ዞን የጎባ ወረዳ ኦሮሚያ ልማት ማህበር ጽ/ቤት

Dead Line: 2016-08-05

 

Tender Detail:

 




በባሌ ዞን የጎባ ወረዳ ኦሮሚያ ልማት ማህበር ጽ/ቤት የጎባ ወረዳ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ማዕከልን ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ተጫራቾች፡-

  1. ለተጠየቁት ግንባታዎች ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የንግድ ፍቃዳቸውን ያሳደሱና ዋናውንና ኮፒውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

  2. በGC ደረጃ 8ና ከዚያ በላይ ወይም በBC የሆነ እንዲሁም ለጥቃቅንና አነስተኛ ማህበር በግንባታ ስራ ላይ ፍቃድ ያለው፡፡

  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

  4. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ፋይናሻሉን እና ቴክኒኩን ለየብቻ በአንድ ኮፒ ማዘጋጀትና እንዲሁም የጨረታውን ማስከበሪያ ሲፒኦ (C.P.O) በኦርጅናል ሰነድ ውስጥ መቀመጥ ይኖርበታል፡፡

  5. ተጫራቾች ለውድድር ካቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (C.P.O) በጎባ ወረዳ ኦሮሚያ ልማት ማህበር ጽ/ቤት ስም በማስያዝ ከሰነድ ጋር ታሽጎ መቅረብ አለበት፡፡

  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 (ሃያ አንድ) ተከታታይ ቀናት ከጎባ ወረዳ ኦሮሚያ ልማት ማህበር ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 12 መግዛት ይቻላል፡፡

  7. ተጫራቾች ለተጠየቁት የግንባታ ፈቃድ እና ከላይ የተጠቀሱትን ዶክመንቶች በሙሉ ጨረታው በሚከፈትበት እለት ኦሪጅናሎቹን ዶክመንቶች ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

  8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ በ3፡30 ሰዓት የጨረታው ሰነድ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ገብቶ ይታሸግና በዚሁ እለት ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጎባ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡

  9. የጨረታው መክፈቻ ቀን በመንግስት የስራ ቀን የማይውል ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፤

10. ጽ/ቤት ሌላ አማራጭ ካገኘ በሙሉም ሆነ በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

11. እያንዳንዱ የፕሮጀክት ሰነድ የሚሸጥበት ዋጋ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ ይሆናል፡፤

ተጫራቾች የጨረታውን ሙሉ ሁኔታ (ገጽታ) ከጨረታ ሰነድ መረዳት ይችላሉ፡፡

ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ ፡- በስልክ ቁጥር 022661 13 84 መደወል ይችላሉ፡፡