Tenders

 

Type: Construction

 

Organization: የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

Dead Line: 2016-10-12

 

Tender Detail:

 




የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለአዳማ ቅርንጫፍ የጥገና እና የማሻሻያ ሥራ ለማሰራት በግንባታ ስራ ላይ የተሰማሩ በደረጃ 4 እና 5 ፍቃዳቸውን ያሳደሱ፣ ከመሠረተ ልማት ሚኒስቴር የምዝገባ የምስክር ወረቀት የሚያቀርቡ ድርጅቶችን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም፦

1. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ የሥራ ተቋራጮች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00/ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፋሲሊቲዎች አስተዳደር በሚገኘበት ቫቲካን ኤምባሲ ወረድ ብሎ በቀድሞ ሚድሮክ ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 305 ህንፃ ግንባታ ክፍል መስከረም 12 ቀን 2009 ዓ.ም.. ዓ.ም. ጀምሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡

2. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የቴክኒካል ሰነድ ዋናውንና አንድ ፎቶ ኮፒ እንዲሁም የዋጋ ሰነድ ዋናውንና አንድ ፎቶ ኮፒ (በማሽን ኮፒ) ሰነዶችን ለየብቻ የፕሮጀክቱን ስም በመጥቀስ በሰም በታሸገ ኢንቭሎፕ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ለዚህ አገልግሎት በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ እስከ ጥቅምት 02 ቀን 2009 ዓ.ም. ከቀኑ 4፡00 ሰዓት በፊት በማስመዝገብ ማስገባት አለባቸው።

3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሰነድ ( BID BOND) ብር 25,000.00 / ሃያ አምስት ሺህ ብር/ በባንክ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (unconditional Bank guarantee) ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡

4. ተጫራቾች ጨረታውን ሲገዙ የንግድ ፍቃድ፣ የሥራ ፍቃድ፣ የታክስ ከፋይነት ማስረጃ (ቲን ሰርተፍኬት) እና ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ማቅረብ አለባቸው፡፡

5. ጨረታው ጥቅምት 02 ቀን 2009 ዓ.ም. ዓ.ም. ከቀኑ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፋሲሊቲዎች አስተዳደር በሚገኝበት ቫቲካን ኤምባሲ ወረድ ብሎ በቀድሞ ሚድሮክ ህንፃ ላይ በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡

6. ባንኩ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0113 – 20 45 88/72 28 72

                                                   
                                                           የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ