Tenders

 

Type: Autos

 

Organization: ትምህርት ሚኒስቴር

Dead Line: 2016-10-09

 

Tender Detail:

 

 

 


ትምህርት ሚኒስቴር ለሚያስገነባቸው አስራ አንድ አዲስ ዩኒቨርሲቲዎች ለግንባታ አገልግሎት የሚውሉ የተለያየ መጠን ያላቸውን የአርማ ብረቶች ከአዲስ አበባና አካባቢው ወደ ተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በዘርፉ በተሰማሩ አጓጓዥ ድርጅቶች ማጓጓዝ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ተጫራቾች፡-

  1. በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የተመዘገቡ እና ማስረጃ የሚያቀርቡ፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የሀገር ውስጥ ገቢ ክሊራንስ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
  2. ጨረታው የሚከናወነው በግልጽ ጨረታ ስነስርዓት ነው፡፡
  3. ፍላጎት ያላቸው ብቁ ተጫራቾች ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል መጫረት ይችላሉ፡፡
  4. የተሟላ የጨረታ ሰነድ ማንኛውም ፍላጎት ያለው ተጫራች የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በጥሬ ገንዘብ በመክፈል ከትምህርት ሚኒስቴር አስራ አንዱ ዩኒቨርሲቲዎች ግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ማግኘት ይቻላል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን እስከ ጥቅምት 9 ቀን 2009 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ትምህርት ሚኒስቴር አስራ አንዱ አዲስ ዩኒቨርሲቲዎች ግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት በመቅረብ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ሁሉም ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የኢትዮጵያ ብር 50,000.00 (ሀምሳ ሺህ ብር) ያቀርባሉ፡፡ ዘግይቶ የቀረበ ጨረታ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ ጨረታው ጥቅምት 9 ቀን 2009 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት የተጫራቾች ወኪሎች በተገኙበት በቢሮ ቁጥር 150 ይከፈታል፡፡
  6. መስሪያቤታችን የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  7. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 156 4052 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር