Tenders

 

Type: Multiple Items

 

Organization: የአዲስ አበባ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤታች

Dead Line: 2016-11-10

 

Tender Detail:

 



የአዲስ አበባ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤታችን ከታች የተዘረዘሩትን ግዥዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

  1. የእቃ ወጪ መጠየቂያ እና የተመላሽ እቃ ደረሰኝ ህትመት አገልግሎት ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 007/2009

  2. የትርጉምና እና ፎቶ ኮፒ አገልግሎት ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 008/2009

ስለሆነም በዘርፉ የተሰማሩ የ2009 ዓ.ም የታደሰ ሕጋዊ የንግድ  ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ እና በድረ ገፅ ላይ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ኮፒ አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች 6 ኪሎ አካባቢ በሚገኘው አ/አ ትምህርት ቢሮ አዲስ ህንፃ በሚገኘው በፕ/ጽ/ቤት 7ኛ  ፎቅ ቢሮ.ቁ 706 በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) መውሰድ ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች ለጨረታ መስከበሪያ የሚሆን ለእያንዳንዱ ጨረታ ብር 5000 (አምስት ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO)   ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

ጨረታው ህዳር 1 ቀን 2009 ከጠዋት 4፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህግዊ ተወካዮች በተገኙበት በፕ/ጽ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡

ፕሮጀክት ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አዲስ ህንፃ (6 ኪሎ አካባቢ)

ስልክ ቁጥር፡- 011-154 04 63