በረዶን በመጠቀም የቆዳችንን ውበት እንዴት መጠበቅ ይቻላል

በረዶን በመጠቀም የቆዳችንን ውበት እንዴት መጠበቅ ይቻላል?

 

 

የሰውነት ቆዳን ውበት ለመጠበቅ በረዶን መጠቀም በአሁኑ ጊዜ በስፋት ሲተገበር ይስተዋላል።

በዚህ መንገድ ውበትን መጠበቅም በበርካታ የውበት በጠበቂያ ሳሎኖች ባለው ጠቀሜታዎች አማካኝነት በስፋት በጥቅም ላይ ይውላል።

የቆዳችንን ውበት ለመጠበቅ ይረዳን ዘንድም በተለይም የፊት ቆዳችንን ጠዋት እና ማታ በበረዶ ማሸት የመከራል።

ቆዳን በበረዶ አድርጎ በስሱ ማሸትም ለስላሳ ቆዳ እንዲኖረን ያደርጋል፣ የደም ዝውወርን በማፋጠን የቆዳችንን ጤንነት ለመጠበቅ ያስችለል እንዲሆም የቆዳ መቆጣት፣ መኮማተር እና መሸብሸብን ይከላከላል።

በበረዶ የፊት ቆዳ ውበትን መጠበቂያ መንገዶች

በመጀመሪያ የፊታችንን በደንብ መታጠብ።

በመቀጠል በረዶ ወስደን በንጹህ ስስ ጨረቅ በመጠቀም በረዶውን በፊታችን ላይ እያመላለስን በስሱ ማሸት።

በተለያዩ የፊታችን ክፍሎች ላይ እያዘዋወርን ከአንድ እስከ ሁለት ደቂያ ማቆየት።

በአፍንጫችን ስር ላለው ቦታ ላይ ጥንቃቄ በማድረግ ሙሉ የፊታችን አካላት ላይ በረዶውን እያዞርን ማሸት ይኖርብናል።

በስተመጨረሻም የቆዳ በሽታን ለመከላከል በሚጠቅሙ ትሪትመት ቅባቶች ፊታችንን ማሻሸት።

ቆዳችንን በበረዶ ማሻሸትን ስናከናውን ከ15 ደቂቃ በላይ ማሸት አይኖርብንም።

 

ምንጭ፦ organichealth.co