Tenders

 

Type: Furniture

 

Organization: የባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት

Dead Line: 2016-06-10

 

Tender Detail:

 






በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ለተገነባው የወረዳ 7 ላይብረሪ የፓርቲሽን እና ቀሪ ስራ በብረታ-ብረት እና እንጨት ስራ ዘርፍ ለተደራጁ ማህበራት ከአነስተኛ ጀማሪ እስከ ታዳጊ መካከለኛ የደረጃ እድገት ያላቸው እና የCOC ምዘና ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ ማህበራትን በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ለመስራት የሚያስፈልጉትን ግብአቶች አቅርቦ የሚሰራ የተሰጣቸውን የደረጃ እድገት እና የ COC ምዘና ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ ማህበራት በጨረታው ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ በሙሉ በአቃ/ቃ/ክ/ከተማ የባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር በአካል በመቅረብ ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ሰነዱ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት እለት አንስቶ ለአስራ አምስት (15) የስራ ቀናት መጥታችሁ መውሰድ የምትችሉ ሲሆን የወሰዳችሁትን ሰነድ ዋጋ ሞልቶ የመመለሻ ጊዜ ጨረታው አየር ላይ በዋለ በአስራ ስድስተኛው የስራ ቀን መሆኑን እየገለጽን በዚያው እለት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 4፡00 ሰዓት በክ/ከተማው በፐ/ሠ/የሰ/ሀ/ል/ጽ/ቤት በግ/ን/አስ/ጠ/አገ/ደ/የስ/ሂደት ሰነድ ማስገቢያ ሰአት ሲሆን በዚያው ቀን ልክ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም ታዛቢዎች ባሉበት ጨረታው የሚከፈት መሆኑን እንግልጻለን፡፡

ማሳሰቢያ፡-

1ኛ. ከተደራጁበት ክ/ከተማ በእጃቸው ላይ ስራ አለመኖሩንና ስራም ካላቸው ከ70% በላይ ማጠናቀቃቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ወይም መረጃ ከመንግስት ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

2ኛ. አሸናፊ ማህበራት ከተደራጁበት የጥ/አ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለቅድመ ክፍያ ዋስትና ማቅረብ አለባቸው፡፡

3ኛ. ከተደራጁበት ክ/ክ የጥ/አ/ኢ/ል/ጽ/ቤት የተሰጣቸውን የደረጃ እድገት ኮፒና ኦርጅናል ማቅረብ አለባቸው፡፡

4ኛ. በአቃቂ ቃሊ/ክ/ከተማ ውስጥ በእጃቸው ስራ ያላቸው ማህበራት በሙሉ በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ለሚወጡ ጨረታዎች ለመሳተፍ የያዙት ስራ ከ70% በላይ ማጠናቀቃቸውን ከአቃ/ቃሊቲ ክ/ከተማ የመንግስት ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

ጽ/ቤቱ ስርዝ ድልዝ ሰነድ የማይቀበልና ከውድድር ውጭ የሚያደርግ መሆኑን እየገለጽን ማንኛውም ተጫራች የወሰደውን ሰነድ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ በሰም በማሸግ ለየብቻ በፖስታ አሽገው ኦርጅናሉ ላይ ኦርጅናል ኮፒዎቹ ላይ ኮፒ በማለት ጽፈውበት ማቅረብ እንዳለባቸው እንገልፃለን፡፡

ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- በስልክ ቁጥር፡- 0118898974

የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ

የባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት