Tenders

 

Type: Multiple Items

 

Organization: የፌደራል በጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ

Dead Line: 2016-09-23

 

Tender Detail:

 

 

 

የተዘጉና በስራ ላይ ያሉ የብሩህ ተስፋ ራዕይ መንደር በኢትዮጵያ፣ ወርልድ ካውንስል ኦፍ ክሬዲት ዩኒየንስ፣ ተስፋ ኅብረተሰብ አቀፍ ቱሪዝምና ጆንሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ ሴንተር ፎር ኮሚኒኬሽን የተባሉ ድርጅቶች ሲጠቀሙባቸው የነበሩ የተለያዩ አገልግሎተ የሰጡ የቢሮ ዕቃዎችና ኢንተርናሽናል አዶፕሽን ጋይድስ እና ሜድስን ዱ ሞንድ የተባሉ ድርጅቶችን 2 መኪናዎች ኤጀንሲው የተረከባቸው ስለሆነ ኤጀንሲው ንብረቶቹን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡- ተጫራቾች

  1. ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ንብረቶቹ በሚገኙበት አድራሻ ቃሊቲ ከማሰልጠኛ አለፍ ብሎ ከአድማስ ዩኒቨርሲቲ አጠገብ በስተቀኝ በሚያስገባው መንገድ 300 ሜትር ገባ ብሎ በሚገኘው ኤጀንሲው በተከራየው መጋዘን ውስጥ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት ድረስ መመልክ ይችላሉ፤
  2. ተጫራቾች የሚገዙትን ንብረት ወይም ተሽከርካሪ ጠቅላላ ዋጋ 20 በመቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) አሰርተው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጪ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡
  3. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው ለአሸናፊዎች ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን፣ ለተሸናፊዎች የጨረታው ውጤት እንደፀደቀ ይመስላቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች የንብረቶቹን ዝርዝር የያዘው ሰነድ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ () ስር የሚገዙበትን ዋጋ በአሃዝና በፊደል ያለ ስርዝ ድልዝ ገልጸው በታሽገ ኤንቨሎፕ (ፖስታ) አዲስ አበባ ከተማ ስታዲየም አካባቢ ቤተዛታ ሆስፒታል ፊት ለፊት ይኃ ሲቲ ሴንተር 11ኛ ፎቅ በሚገኘው የኤጀንሲው ዋና መ/ቤት ግዢና ፋይናንስ ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውሰጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ነገር ግን የሚሰጡት ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ከጎኑ በተጫራቹ መፈረም አለበት፡፡
  5. ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር (10) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የጨረታውን ሰነድ ማስገባት አለባቸው፡፡
  6. አሸናፊ ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸውን ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ10 ቀናት ውስጥ ገንዘቡን ገቢ በማድረግ በ15 ቀናት ውስጥ ንብረቱን የመረከብ ግዴታ አለባቸው፡፡ ይህ ካልሆነ ያስያዙት ገንዘብ ለኤጀንሲው ገቢ ይሆናል፡፡
  7. ተጫራቾች ከኤጀንሲው ግዢና ፋይናንስ የንብረቶቹን ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ የማይመለስ ብር ለቢሮ ዕቃዎች 50 (ሀምሳ ብር) እና ለተሽከርካሪዎች 150 (አንድ መቶ ሀምሳ ብር) እየከፈሉ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር (10) ተከታታይ የሥራ ቀናቶች ድረስ መግዛት ይችላሉ፡፡
  8. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር (10) የሥራ ቀናት ክፍት ሆኖ በ10ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዲስ አበባ ከተማ ስታዲየም አካባቢ ቤተዛታ ሆስፒታል ፊት ለፊት ይኃ ሲቲ ሴንተር 11ኛ ፎቅ በሚገኘው የኤጀንሲው ዋና መ/ቤት ስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
  9. ተጫራቾች ስለአሻሻጡ ዝርዝር ሁኔታ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ከተያያዘው የተጫራቾች መመሪያ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  10. ድርጅት ለአሻሻጡ የተሻጡ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- በስልክ ቁጥር 011 5582446

የፌደራል በጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ