የአበባ ጎመን ጥብስ አስራር

የአበባ ጎመን ጥብስ አስራር

አስፈላጊ

1አበባ ጎመን

1/2 የሻይ ማንኪያ ጨው

1/4 የሻይ ማነኪያ ቁንዶ በርበሬ

2 ዕንቁላል

1 የሾርባ ማነኪያ ፉርኖ ዱቄት

1 ራስ ቃሪያ

ዘይት ለመጥበሻ ያክል

 

አስራር

አበባ ጎመኑን አጥበን እንለየዋለን

ጨው ባለበት ውሃ ውስጥ ካገነፈልነው ቤላ አውጥተን ውሃውን ማጠንፈፍ

ዕንቁላሉን ከመታን በኁላ ቁንዶ በርበሬውን ጨምሮ መቀላቀል

የአበባ ጎመኑን እንቁላሉ ውስጥ እየነከርን ፉርኖ ዱቄቱ ላይ ማንከባለል

በመካከለኛ ሙቅት  መጥበሻ ላይ ዘይቱን ጠብ አርጎ መጥበስ እና ቃሪያውን ከትፎ መጨመር   እናም በትኩሱ መመገብ

ምንጭ፡- ከባህላዊ ምግብ አዘገጃጀት መጻፍ የተወሰደ