እኔ ወደዚህ ሙያ ስገባ ይህን አገኛለሁ እንዲህ እሆናለሁ ብዬ አይደለም

ድምጻዊ ካሳሁን ታዬ(ሰራ)

 

Image result for ድምጻዊ+ካሳሁን+ታዬ+(ሶራ)

 

ባውዛ፡- ካሣሁን እንኳን ደህና መጣህለባውዛ ቃለ መጠይቅ።

ካሣሁን፦ በመጀመሪያ ለባውዛ የሚዲያዝግጅት ጋር እንኳን ለመገናኘት አበቃንእላለሁ። እንዲሁም የባውዛ አንባቢዎችን

ጭምር ማለቴ ነው።

ባውዛ፡- ምን አልባት ብዙዎች አንባቢዎቻችንይሄንን አርቲስት ለማወቅ ናፍቆት ውስጥእንደነበሩ ይሠማኛል። ካሣሁን እንዴት ወደዘፋኝነት ሙያ ልትገባ ቻልክ? ያነሣሣህንነገር ብትገልፅልን። መቼም አንድ ሠውአርቲስት ለመሆን ሲነሣ የራሡ የሆነ ሮል

ሞዴል አለው እስኪ ባንተ አንደበት እንዴትይገልፃል።

ካሣሁን፦ ያው እኔ እንግዲህ ወደዚህ ሙያውስጥ እንድገባ ካነሣሣኝ ነገሮች ብዙን ጊዜ በቤተሠብ በኩል ይዘኸው የመጣኸው ነገር ሊኖር ይችላል ግን በዚህ ሙያ ካነሣሡኝ ነገሮች አንዱ በልጅነቱ ጀምሮ ሲጫወት በጣም የምወደውና የማደንቀው አርቲስት አንዱ ይሁኔ በላይ ነው። የሱ ዘፈኖች በወጡበት ጊዜ እና አንቱየዋ ያገሬ ልጅ ባለጋሜን …. ስሰማ በጣም ከምወዳቸውውስጥ አንዱ ይሁኔ በላይ ሲሆን እንዲሁም እነ አርቲስት ይርጋ ዱባል ሌሎቹም ለኔበአራያነት የምጠቅሳቸው ናቸው።

ባውዛ፡- ይሄንን ስራ በሀገራችን ብዙ አርቲስቶች አድገውበት ሲያምሩበት አናይም ሲደነቁበት እንሠማለን እናምስትጀምረው ይህን አገኝበታለሁ ብለህ ነው ወይስ የስሜትህ ጉዳይ ሆኖ ነው የጀመርከው?

ካሣሁን፦ እኔ ወደዚህ ሙያ ስገባ ይህን አገኛለሁ እንዲህ እሆናለሁ ብዬ አይደለም የጀመርኩት ሌሎችን ሣይ ሙያዊ ፍቅር ገፋፍቶኝ ነው። እኔ ብዙውን መጫወት የምወደው የባህል ዘፈኖችን ነው በተለይ ወደ ሠሜኑ አካባቢ ወደ ዋግና ሰቆጣ የላሊበላ ባህሎች በጣም ወድጀው ስለምጫወት በጣም ተዋጥቶልኛል ብዬ አስባለሁ።

ባውዛ፦ ሶራ ቋንቋው እንዴት ተገኝ፣ ግጥሙንም ዜማውንም እንዴት አዋሃድከው?

ካሣሁን፦ ብዙዎች አድማጮች ይህን ዜማ የተረዱት ይመስለኛል ሶራ ማለት ሶስት ትርጉም ሰጥተነዋል። እንዴት መጣ ለሚለው ከላስታ ከቅዱስ ላሊበላ ዘመን ጀምሮ የመጣ ነው የምንጣፍ ስያሜ ነው። ይህንን የሰየሙት ላስታ ውስጥ 11 ነገስታቶች ነግሠዋል ከነዚያ ውስጥ አንዱ ቅዱስ ላሊበላ ነው። በዚያ ዘመን የተሠየመ ነው። በሌላ ጐኑ ሶራ ማለት የላም ስም ያገር ስምም ነው ልዩነቱ ዥጉርጉር ቀለም ያላቸው ውብ ቀለም ያላቸው ሁሉ ሶራ ተብለው እንደሚጠሩ መረጃዎች ያስረዳሉ።

ባውዛ፡- በጣም ጥሩ ነው! በዚህ አይነት እንግዲህ ሶራ ታላቅ ሶራ እንበለዋ!?

ካሣሁን፦ ይቻላል!

ባውዛ፡- ብዙውን ጊዜ አንድ ሠው በሚሠራው ጥሩ ስራ በቅፅል ስም ይጠራል እንዲያውም ስሙ እንዳለ ይሆንና ስራው በአባትነት ወይም በመለያነት ይለመዳል። አንተም አሁን በቅፅል ስምህ ካሣሁን ሶራ እየተባልክ ነው። እንዴት ነው ቅፅል ስምህን ወድኸዋል ወይስ ካሣሁን ሶራ ሲሉህ እንዴ! አንተ(ች) እኔ እኮ ያባት ስም አለኝ ብለህ ታውቃለህ?

ካሣሁን፦ አላውቅም! እንዲያውም ካሣሁን ሶራ ብለው ሲጠሩኝ እጅግ ኩራት ነው የሚሠማኝ ምክንያቱም ካሣሁን ታዬ ያባቴ መጠሪያ ነው ካሣሁን ሶራ ደግሞ እንደገና የተወለድኩበት የህዝብ ፍቅር ብሎም እንጀራም ያገኝሁበት ስለሆነ በጣም ኩራት ይሠማኛል።

ባውዛ፡- ልክ ነው የሚያስጠራ ሥራ መስራት ያስደስታል ልጅም እኮ ያስጠራል ታዲያ ከአሁን በኋላስ የበለጠ የሚያስጠራ ስራ ለመስራት ዝግጅትህ ምን ይመስላል?

ካሣሁን፦ ከአሁን በኃላ እንኳን አንዴ በሶራ ስም ተተክሏል የሚቀጥለውም ልጅ ቢወለድ እንደመጀመሪያው ልጅ የመጀመሪያው ምዕራፍ ይዞት የሄደው ሶራ ነው። የዘላለም መጠሪያዬ የሚመስለኝ የበለጠ ስራ እንኳን ብሠራ እንደመጀመሪያው ላይሆን ይችላል ስራው ግን ሊወደድ ይችላል።

ባውዛ፡- እሺ ካሣሁን እንዲህ ምን እያሠበ ነው እንደዚህ የሚወደውን ህዝብ እንዴት ይጠብቁት የካሣሁን ቻናሉ የትኛው ነው?

ካሣሁን፦ ቻናሉ እንኳን አንድ እና አንድ ነው ካሣሁን የባህል ዘፋኝ ነው። ይህንን ባህላችንን በተሻለ መልኩ እያጠናከርን መግፋት እንጂ ወደ ዘመናዊ የምገባበት መንገድ የለም።

ባውዛ፡- አሁን ብዙ ሰዎች እንደሚስማሙበት ደብዘዝ ብሎ የነበረውን ባህላችንን ገና ታይቶ እንዳላለቀ “ሶራ” አንድ ነገር ጠቁሟል። የሚሉ ሰዎች አሉ አንተ ጠብቀህ ነበር?

ካሣሁን፦ አዎ ባህላችን ባንድ ወቅት ጥሩ ነገር ይዞ መጥቶ ነበር። እንዳጫወትኩህ እኔ ይርጋ ዱባለ ከጐንደር እና ማሪቱ ለገሠ ከወሎ፣ ከግሼ አባይ ደግሞ እነ ይሁኔ በላይ፣ ሰማኸኝ በለው እነኚህ ሁሉ ከኛ ክልል ውስጥ የባህል አምባሣደሮቻችን ናቸው። እነሱ ይዘውት የመጡት የባህል አያያዝ ትንሽ እየተለወጠ ነ በ ር ። አምባሣደሮቻችን ናቸው። እነሱ ይዘውት የመጡት የባህል አያያዝ ትንሽ እየተለወጠ ነበር። አሁንም እኛም ደግሞ በተቻለን ወደ ሚዲያ ይዘን መጥተናል ህብረተሠቡም ባህልን የኔ ነው ብሎ ተቀብሎታል። የበለጠ እየወደደው መጥቷል ስለዚህ የሚቻለንን ሁሉ በማድርግ የኛ መገለጫ የሆነውን ቱባ ባህላችንን እንጠብቃለን? በተሰጥኦአችን ላድማጫችን አናደርሳለን።

 ባውዛ፡- ሶራን እያዳመጥን አብረውህ የሚጨፍሩትን ተወዛዋዦች ስንመለከት ለየት ያለ ስሜትና ደስታ ለተመልካቹ ሲረጩ ይታያሉ የሶራን ዘፈን እንዴት አገኘኸው። ተወዛዎዦችንስ እንዴት አሠባሰብካቸው?

 ካሣሁን፦ የሶራ ስብስቡ በጣም ከበድ ይል ነበር። ምክንያቱም ሁላችንም በተለያየ ቦታ ነበር የምንኖረው ግን የባህል ጉዳይ ነውና ባህል ፍለጋ ስንዟዟር እነኚህና ውጤት ድንቅ ተወዛዋዦችን አገኘን እና ላስቱን እና ዘላለምን ከላስታ ላሊበላ አገኝን ወደ ዋግሞራ ስቆጣ ስንሄድ እነ መኳንንትን እና ሌሎችን በቡድኑ ውስጥ ያሉትን በሙሉ አገኘናቸው። በካሜራችን ያዝናቸው እና ስራውን ጀመርን ዘፈኑ ካማረ የውዝዋዜው ጥበብ ታክሎበት ተቀባይነትን ካገኝን በኃላ ነው ጥንካሬውን ያወቅነው እንደዚህ ይሆናል ብለን አላሠብንም ነበር። እነኝህ ልጆች ከዘፈኑ በላይ ትልቁን ቦታ የሚሠጣቸው ናቸው። እኔ ምንም ዘፋኝ ብሆንም የተለየ ነገር አልዘፈንኩም የተለየ እንቅስቃሴና የተለየ ጭፈራ ይዘው የመጡ እነሱ ስለሆኑ ትልቁን ቦታና ድጋፍ ለተወዛዋዦቼ ነው የምሰጣቸው።

 ባውዛ፡- መቼም ባነጋገርኳችሁ ጊዜ በመካከላችሁ ያየሁት ነገር እነሱም ላንተ የተለየ ክብርና ቦታ እየሠጡ አንተን ሰበብ ያደርጋሉ። አንተም ደግሞ ለእነሱ ያለህን አድናቆት በጣም ደስ ይላል። በመጨረሻ ላነሣው የምፈልገው ጥያቄ ትውልድህ የት ነውተወልደህ ስላገኘሁህ ነው። የት አካባቢ ተወለድህ አደግህ?

ካሣሁን፦ እኔ የተወለድኩት በሰሜን ጎንደር ሃሙሲት በለሳ ይሏታል ትውልዴ እዚያ ሲሆን በሌላ ጐን ባባቴ በኩል ደግሞ ወሎ ሰቆጣ ውስጥ ነው ያደግሁት በዋነኛነት በእናቴ ጐንደር በአባቴ ሰቆጣ ነኝ እኔ ሁለቱን በዘፈን አገናኝቻቸዋለሁ።

ባውዛ፡- ካሣሁን ወደፊት ምን ምኞት አለው? የምንኖርባትን አለም ወደፊት ምን ቢሆን ደስ ይለዋል?

ካሣሁን፦ ለወደፊት አገራችን ሌሎች ያደጉ ሀገሮች ከደረሡበት ደረጃ ደርሣ ማየት። አርቲስቶች ደግሞ የበይ ተመልካች ሣይሆኑ በስራቸው ተጠቃሚ ሆነው የህዝብ ፍቅራቸውን ለዘላለም አፅንተው እንዲኖሩ እፈልጋለሁ። ስለ ባውዛ ጋዜጣችሁ ደግሞ ማለት የምፈልገው ከዚህ በፊት በአሜሪካ አገር የሚታተም መሆኑን ሌሎች አርቲስቶችም የዚህ ጋዜጣ ኢንተርቪው መስጠታቸውን ወደ አሜሪካ ጎራ ያሉ ሁሉ ታዳሚ መሆናቸውን ሲናገሩ እሠማ ነበር። አሁን እኔን እዚሁ በባውዛ ብርሃን ፈልጋችሁ አገኛችሁኝ። በጣም አመሠግናለሁ ባውዛ ማለት ብርሃን የሚዘራ ማለት ነው እና ባውዛ የበለጠ አድጐ ከጋዜጣ ወደ ቴሌቪዥን እያደገና የሙያተኞችን የስራ ውጤት ፊት ለፊት የምታሣይ እንድትሆን በኢንተርኔት በ bawza.com ብዙ የሚታዩ የሚያስተምሩ የሚያዝናኑ ነገሮች እንደምታስተላልፍ አውቃለሁ ዋና አዘጋጁም የኔው የዘፈን ፍላጐቴ አነሣሽ ያርቲስት ይሁኔ በላይ በመሆኑ እጅግ እንደምወዳትና ብዙ እንደምጠብቅ ልገልፅ እወዳለሁ፡- እንግዲህ ውድ የባውዛ አንባቢዎች በሩቁ በቴሌቭዥን መስኮት የምታዩትን አርቲስት በባውዛችን አፈላልገን ለቃለ መጠይቅ አብቅተናል ካሣሁን በጣም ጥልቅ ነው ከመሬት ተነስቶ ሶር አላለም። ከካሣሁን ለወደፊት ብዙ እንጠብቃለን፡፡

ምንጭ፡- ባዉዛ ጋዜጣ 2004ዓ.ም