ስኬትን ምን ያህል እንፈልገው ይሆን?

 ስኬትን ምን ያህል እንፈልገው ይሆን?

የhappy ምስል ውጤት

አንድ ሰው ከመጠን በላይ ስኬታማ መሆን ይመኝ ነበርና ወደ አንድ አዋቂ ዘንድ ይሄዳል። ለአዋቂውም ታላቅ ሰው መሆን እንደሚፈልግ እና እርዳታውን እንደሚሻ ይነግረዋል። አዋቂውም መልሶ “ እሺ ስኬታማ ሰው መሆን ከፈለግክ ነገ ባህር ዳርቻ እጠብቅሃለው በጠዋቱ ና” ሲል መለሰለት። ሰውየው ግራ ተጋብቶ “እኔ ስኬታማ ሰው አድርገኝ አልኩኝ እንጂ ዋና አስተምረኝ አላልኩሁም እኮ” ይለዋል።

 

አዋቂውም “ወንድሜ ስኬታማ መሆን እፈልጋለው ነው ያልከው …… ነገ ጠዋት ከባህር ዳርቻው ጋር እንገናኝ” ብሎት መልሱን ሳይጠብቅ ጥሎት ሄደ። በበነጋታው ሰውየው ከባህሩ ዳርቻ ተገኘ ፤ሙሉ ልብሱን ሽክ ብሎ ነበር የመጣው

ሰላምታ ከተለዋወጡ በኋላ ሰውየው መጀመሪያ የጠየቀውን ጥያቄ አንደገና ጠየቀ “ስኬታማ ሰው ለመሆን ምን ማድረግ አለብኝ?” አለው። አዋቂው በዝምታ ተመለከተው… “ና ተከተለኝ” ብሎ ወደ ባሕሩ ተጓዙ…ሰውየው ግራ ገባው..ነገር ግን አዋቂ የተባለው ሰው እጅግ የተከበረ ነበረና የሚሰራውን ያውቃል በማለት ዝም ብሎ ተከተለው….ወደ ባሕሩ ዘለቁ…መጀመሪያ ውሃው እስከ ጉልበታቸው ደረሰ…ቀጥሎ እስከ ወገባቸው….ቀጥሎ እስከዳረታቸው…..የሰውየው ልብ ተረበሸ….ስኬታማ መሆን ከዚህ ጋር ምን እንደሚያገናኘው ግራ ቢገባው “ይህ ነገር ስኬታማ ከመሆን ጋራ ምን አገናኘው?” ሲል ጠየቀ

አዋቂውም “ስኬታማ መሆን እፈልጋለው ነው ያልከኝ ወዳጄ?” አለው

ሰውየው “አዎ” ሲል መለሰ

አዋቂው የሰውየውን መልስ እንደሰማ የሰውየውን ጭንቅላት ይዞ ወደባሕሩ ደፈቀው። ሰውየው እራሱን ለማዳን ቢንፈራገጥም አልቻለም….አዋቂው የሰውየውን ጭንቅላት ለሴኮንዶች ውሃ ውስጥ ካቆየው በኋላ ቀና አደረገው…ይሄኔ ሰውየው በሃይል እየተነፈሰ

“እኔ….ስኬታማ አድርገኝ ባልኩኝ ለምን ልትገለኝ ፈለግክ?” ሲል ጠየቀ

“ስኬታማ መሆን ትፈልጋለህ?” አለው አንገቱን እንደያዘ

“አዎ”…ብሎ ሲመልስ ደግሞ ከባሕሩ ነከረው፤ እንደቅድሙ ትንሽ አየር እስኪያጥረው ካቆየው በኋላ ቀና አድርገው እንዲህ ሲል ጠየቀው

“አሁን በዚህች ቅፅበት በጣም የምትፈልገው ነገር ምንድን ነው?”

ሰውየው..ቁና ቁና እየተነፈ ….. “አየር” አለ

“አየህ አሁን አየር እንደፈለግከው ያህል….ስኬትን ክፉኛ ካልፈለግካት መቼም አታገኛትም…ይህ ነው የስኬት ሚስጥር” አለና አሰናበተው ይባላል።

 

አንዳንዶች የፈለጉትን ሲያገኙ እናያለን አንዳንዶች ደግሞ እንዳሰቡት ሳይሳካላቸው ይቀራል። የሁለቱን ሰዎች ልዩነት እድል በሚባለው ነገር ልናስታርቀው ብዙ ጊዜ ብንጥርም እውነታ ግን ሌላ ነው…..ስኬት ጥቂቶች ብቻ የሚታደሏት አይደለችም..ሁላችንም እንድንደርስባት በእኩል ቦታ የተንጠለጠለች ፍሬ እንጂ…..እጅግ የተራባት ሰው ማድረግ ያለበትን ሁሉ አድርጎ ያገኛታል….

 

ብዙዎቻችን ስኬታም መሆን ብንፈልግም እጅግ ከስኬት በላይ አብዝተን የምንወዳቸው ሌሎች ጥቃቅን ነገሮች ህይወታችንን ሞልተውታል። ሁሉም ስኬታማ ሰዎች ወደ ስኬት የመጡበት መንገድ ይለያያል፤ አንድ ፍጹም የሚያመሳስላቸው ነገር ቢኖር ግን ሁሉም ይቻላል ብለው ማመናቸውና ላመኑት ነገር ያላቸውን ሁሉ ሳይሰስቱ መስዋት ማደረጋቸው ነው። አሁን በሌሎች ሰዎች አይን “ስኬታማ” ተብለው የሚጠሩ ሰዎች በአንድ ወቅት እንደማንኛችንም አይነት አቅም እና ችሎታ ነበራቸው…የአስተሳሰብ ሁኔታ ግን አንዳችንን ወደ ኋላ አንዳችንን ወደፊት እንድንራመድ አደረገን።

አይምሮዋችን እንደ እርሻ ነው….የዘራንበትን ያሳጭደናል…አይምሮ እኛ ምን እንዝራ ምን እንትከል ግድ የለውም። መሬት በቆሎ ተዘራ ጤፍ ተዘራ ግድ አለው እንዴ?….አናም አይምሮዋችን ላይ መልካሙን ሰብል መርጠን እንዝራ….

ምንጭ፡- ከስኬት ሚስጥሮች