ሳይኮሎጂ | ለራሳችን መንገር የሌለብን 4 ነገሮች

 

ሳይኮሎጂ | ለራሳችን መንገር የሌለብን 4 ነገሮች

 

 

የተለያዩ ችግሮች ውስጥ የምታልፉበት አጋጣሚ ሊኖር ይችላል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ለችግሮቹም ራሣችሁን ተጠያቂ ታደርጉ ይሆናል፡፡ በየትኛውም አይነት ሁኔታ ውስጥ ብትሆኑም ግን ደካማነታችሁን የሚያጎሉና ከሠዎች በታች ሆናችሁ እንድትታዩ የሚያደርጉ ቃላትን መጠቀም የለባችሁም በማለት የሥነ-ልቦና ምሁራን ይመክራሉ፡፡ እነኚህ ቃላት አስተሳሰባችን ላይ አሉታዊ ተፅእኖ የመፍጠር አቅማቸው ከፍተኛ ነው፡ ፡ ለራሳችን የምንናገራቸው አሉታዊ ቃላት ከፍተኛ ጉዳት እንዳላቸው ከሕይወት ልምዴ ተገንዝቤያለሁ የሚሉት የሥነ-ልቦና ባለሙያው ማይክ ቡንድራንት በተለይ የሚከተሉትን ቃላት ለራሳችሁ ፈፅሞ መንገር የለባችሁም ይላሉ፡፡

 

የማልረባ ነኝ

 

ይህ በራስ መተማመናችሁን በቀጥታ የሚገድል አነጋገር ነው፡፡ የማትረቡ ወይም አንዳች ዋጋ የሌላችሁ መሆኑን ለራሳችሁ መንገር አሉታዊ አስተሳሰብ በአእምሯችሁ እንዲሰርፅ የማድረግ ኃይል ስላለው ቃሉን መጠቀም ተገቢ አይደለም፡፡

 

2. አልችልም

 

አንዳንድ ነገሮችን በምትፈልጉት ደረጃ መስራት የማትችሉባቸው ሁኔታዎች በሚፈጠሩበት ጊዜ አቅማችሁን ልትጠራጠሩ ትችላላችሁ፡ ፡ የምታደርጉት ነገር ጥቅም እንደ ሌለው ለራሳችሁ መንገር ለሥራ ያላችሁን የተነሳሽነት ስሜት ይቀንሠዋል፤ አቅማችሁን ያሣጣችኋል፡፡ ይህ አነጋገር እውነታውን ከመግለፅ በላይ ራሳችሁን መልሶ የማጥቃት አቅም አለው፡፡ አንድ ነገር ከመሥራታችሁ በፊት እወድቃለሁ/ አይሣካልኝም ከማለት ይልቅ ደጋግሞ በመሞከር ለውጤት መብቃት እንደምትችሉ ማመን አለባችሁ፡፡

 

3. ሠዎች አይወዱኝም

 

ሠዎች አይወዱኝም የሚለውን ስሜት በአእምሯችን ማስረፅ ሌሎች ከእኛ የተሻሉ እንደሆኑ እንድናስብና ለራሳችን ጥረት ተገቢ ውጤት እንዳንሠጥ ያደርገናል፡፡ በሌሎች ያለመወደድ ስሜት ከተሠማን ደግሞ ለራሳችን የምንሠጠው ክብርም ይቀንሳል::

 

4. ለውጥ ማምጣት አልችልም

 

አንድን ነገር ለመለወጥ አቅማችሁ ካልፈቀደ ራሣችሁን አታስገድዱት፡፡ ፍፁም መሆንንም ከራሣችሁ አትጠብቁ፡፡ በተለያዩ ርዕሠ ጉዳዮች ላይ የምትሠጧቸው ሀሳቦች የራሳቸው አዎንታዊ ተፅእኖ አላቸው፡፡ ስለዚህ ‹ለውጥ ማምጣት አልችልም›› የሚለው ቃል ለራሳችሁ መንገር ከሌለባችሁ አሉታዊ ቃላት መካከል አንዱ ነው፡፡

 

በአጠቃላይ ስሜታችሁን የሚጎዱ እንዲህ ዓይነት ቃላትንና አነጋገሮችን መጠቀም ትታችሁ አንደበታችሁን በመጠበቅ በየዕለቱ ለምታከናውኗቸው ተግባራት ትኩረት በመስጠት ውጤታማ መሆን ትችላላችሁ፡፡

 

ምንጭ፡- Psychcentral.com