ለቢሮ ውስጥ ሸለብታ ይህንን ቢያደርጉስ?

ለቢሮ ውስጥ ሸለብታ ይህንን ቢያደርጉስ?

ለቢሮ ውስጥ ሸለብታ ይህንን ቢያደርጉስ?

በስራ ሰዓት መሃል ላይ የሚደረግ ሸለብታ የሰራተኛውን አዕምሮ በማነቃቃት ጥሩ የስራ ባህሪን ለማላበስ እንደሚረዳ ይነገራል።

እንደ ባለሙያዎቹ ገለጻ ሸለብታን ማድረግ በስራ ሰዓት መፍዘዝን ያስቀራል፣ የስራ ተነሳሽነትንና ንቃትን ይጨምራል ከዚህ ባለፈም የተሻለ የስራ አፈጻጸም እንዲኖር ያስችላል።

በዚህ ሃሳብ ብዙ አሰሪዎች ባይስማሙም፥ በቀን የስራ ጊዜ ጥቂት ደቂቃዎችን በሸለብታ ማሳለፍ ለስራውም ሆነ ለሰራተኛው መልካም ስለመሆኑም ነው ባለሙያዎች የሚገልጹት።

ለዚህ ደግሞ በቀን የስራ ሰዓት በተለይም በከሰዓት በኋላው ፕሮግራም፥ እስከ 30 ደቂቃ የሚደርስ ጊዜን ማሸለብ አስፈላጊ ነው ይላሉ።

አብዛኛዎቹ ሰራተኞች ሸለብታን ለማድረግ ደግሞ ጠረጴዛ እና ወንበር የመሳሰሉ የቢሮ መገልገያዎችን ሲጠቀሙ ይስተዋላል።

ይህን ሲያደርጉ ግን የሸለብታ ጊዜው የተቆራረጠና ያልተስተካከለ ሲሆን ይስተዋላል።

ለዚህ ደግሞ አግባብነት ያለው መደገፊያን አለመጠቀምና እረፍቱን የሚወስዱበት ጊዜ ላይ የቢሮው ሁኔታ ወሳኝነት ይኖረዋል።

ባለሙያዎች ግን ሰውነት የሚፈልገውን በቂ ሃይል እና እረፍት በትንሽ ደቂቃ ለማግኘት የሚያደርጉት ሸለብታ ምቹና ውጤታማ እንዲሆን እነዚህን መንገዶች ይከተሉ ብለዋል።

በጥቂት ደቂቃ ጥሩ እንቅልፍ ለማግኘትም፥

ቢችሉ አንድ ቦታ ላይ ጥቂት አረፍ የሚሉበትን ሁኔታ ቢሮ ውስጥ ማመቻቸት፣

ይህን ማድረግ ካልቻሉ ደግሞ በሚለጠጥ እና በሚሳብ ወንበር በመጠቀም እግርና ወገብዎን ቀጥ በማድረግ ለማረፍ መሞከር።

ይህ ሳይሆን ቀርቶ ጠረጴዛንና ወንበርን ያላንዳች ነገር ተደግፎ መተኛቱ ግን ጉዳት አለውና ያንን ያስወግዱ።

መደገፊያውን ማስተካከል አልያም አነስተኛ የአንገት ስር ትራስ መጠቀም፦

ምናልባት ለሰራተኞቹ የሸለብታ ሰዓትን በሚፈቅድ ድርጅት ውስጥ የማይሰሩ ከሆነ ምቹ የእረፍት ጊዜ አይኖርዎትም።

በዚህ ምክንያት ደግሞ የሚሰሩበት ጠረጴዛ እና ወንበር ላይ ወደ ኋላ ለጠጥ አልያም ጠረጴዛዎ ላይ ሁለት እጅዎን ተደግፈው መተኛትወ አይቀርም።

ይህ ግን አዋጭ አይደለም፥ ከዛ ይልቅ ወንበርዎ ላይ ለጠጥ ብለው ለጭንቅላትዎ መደገፊያ የሚሆን በእጅ የምትያዝ እና አነስተኛ ትራስን ቢጠቀሙ።

ለዚህ ደግሞ በ”ዩ” ቅርጽ የተሰራ አነስተኛ የአንገት ትራስን መገልገል፥ በደንብ እንዲያርፉና አንገትዎም ጉዳት እንዳይደስበት ይረዳወታል።

አይንና ጆሮዎን መሸፈን ወይም መጨፈን፦ ለማረፍ ሲሞክሩ አይንዎን ቢጨፍኑም ብርሃን ነገር ካለ መረበሽዎ አይቀርም ምናልባት በሚሰሙት ድምጽም ያሰቡትን እረፍት አያደርጉ ይሆናል።

ለዚህ ደግሞ ከቻሉ አይን ላይ ጣል የሚደረጉ ጥቁር የአይን መከለያ ጨርቆችን መጠቀም እና ሸለብታ ሲያደርጉ አይንዎ ላይ ጣል ማድረግ።

ጆሮዎን ደግሞ የጆሮ ማዳመጫ መሳሪያዎችን ሙዚቃ ነገር ሳይከፍቱ ማስቀመጥ እና ሸለብታ መውሰድ።

ምናልባትም ቢሮ ውስጥ አየር ማቀዝቀዣ ካለ እርሱን ማጥፋት፣ መጋረጃዎችን እስከሚነቁ መጋረድ እና ከውጭ ድምጽ የሚያስገቡ መስኮት እና በሮችን መዝጋት።

ወፈር ያለ ሹራብ ነገር ካለም እርሱን ደረብ በማድረግ የአጭር ጊዜዋን ሸለብታ መውሰድን ባለሙያዎች ይመክራሉ።

ይህን ሲያደርጉ ከሚረብሽ ብርሃንና ድምጽ ራስዎን በማራቅ ጣፋጭ የደቂቃዎች የእረፍት ሰዓትዎን መጠቀም ይችላሉ።

 

 

 

ምንጭ፦ psychologytoday